ዘኍል 5:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ይህ ሰው ካሳውን የሚቀበልለት ዘመድ ከሌለው ካሳው ለእግዚአብሔር ስለሚሆን ማስተስረያ እንዲሆነው ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋራ ለካህኑ ይስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በዳዩ ይመልስለት ዘንድ ለተበዳዩ ሰውዮ ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለጌታ የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሆናል፥ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት የማስተስረያ አውራ በግ ላይ ይጨመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ሰው ቢሞትና ካሳውንም የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን በካህኑ አማካይነት ስጦታው ለእግዚአብሔር ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም ስለ በደል የሚከፈል ዋጋ መሰጠት ያለበት፥ በደል የሠራው ሰው ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕትነት ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋር ተጨማሪ በመሆን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዬው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፤ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ ላይ ይጨመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ይመልስለት ዘንድ ሰውዮው ዘመድ ባይኖረው፥ ስለ በደል ለእግዚአብሔር የሚመልሰው ነገር ለካህኑ ይሁን፥ ይህም ስለ እርሱ ማስተስረያ ከሚደረግበት አውራ በግ በላይ ይጨመር። |
ከተቀደሱ ነገሮች ያጐደለውንም ይተካ፤ የዚህንም ተመን አንድ ዐምስተኛ በላዩ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም ከበጉ ጋራ የበደል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።
በሐሰት የማለበትንም ሁሉ ይመልስ፤ የበደል መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ጊዜ የወሰደውን በሙሉ የዋናውን አንድ ዐምስተኛ በመጨመር ለባለንብረቱ ንብረቱ ይመልስ።