Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 7:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ ‘የኀጢአት መሥዋዕትና የበደል መሥዋዕት አቀራረብ ሥርዐት አንድ ነው፤ መሥዋዕቶቹ የስርየቱን ሥርዐት ለሚያስፈጽመው ካህን ይሰጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የበደል መሥዋዕት እንደ ኃጢአት መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ አለ፤ ያም በእነርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ከእነርሱ ላይ ለራሱ ስለ ሚወስድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ስለ ኃጢአት ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕትና ስለ በደል ስርየት በሚቀርበው መሥዋዕት መካከል ለሁለቱም የሚሠራ አንድ ዐይነት ሕግ አለ፤ ይኸውም የእንስሳው ሥጋ መሥዋዕቱን ለሚያቀርበው ካህን ምግብ እንዲሆን ይሰጣል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የኃጢአት መሥዋዕት እንደ ሆነ እንዲሁ የበደል መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ይወስደዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 7:7
11 Referencias Cruzadas  

ስለ በደል መሥዋዕትና ስለ ኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበው ገንዘብ ግን የካህናቱ በመሆኑ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይገባም ነበር።


በዚህ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ወጣ፤ ጋትንም አደጋ ጥሎ ያዛት። ከዚያም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ፊቱን አዞረ።


ጠቦቱንም፣ የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት በተቀደሰው ስፍራ ይረደው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱ ለካህኑ እንደሚሰጥ ሁሉ የበደል መሥዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው።


የተረፈውም የእህሉ ቍርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ቍርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።


የተረፈውም የእህሉ ቍርባን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ፤ ይህም ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ቍርባን እጅግ የተቀደሰ ክፍል ነው።


ያለ እርሾ መጋገር አለበት፤ በእሳት ከሚቀርብልኝ ቍርባን ይህን የእነርሱ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም፣ እንደ ኀጢአት መሥዋዕትና እንደ በደል መሥዋዕት ሁሉ እጅግ የተቀደሰ ነው።


ስለ ማንኛውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበው ካህን ቈዳውን ለራሱ ይውሰድ።


ነገር ግን ይህ ሰው ካሳውን የሚቀበልለት ዘመድ ከሌለው ካሳው ለእግዚአብሔር ስለሚሆን ማስተስረያ እንዲሆነው ከሚያቀርበው አውራ በግ ጋራ ለካህኑ ይስጥ።


እስኪ የእስራኤልን ሕዝብ አስቡ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉት ከመሠዊያው ጋራ ኅብረት አልነበራቸውምን?


በቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከቤተ መቅደስ እንደሚያገኙ፣ በመሠዊያውም የሚያገለግሉ ከመሥዋዕቱ እንደሚካፈሉ አታውቁምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos