ዘኍል 3:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሊብናና የሰሜኢ ጐሣዎች ከጌርሶን ወገን ናቸው፤ እነዚህ የጌርሶን ጐሣዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌድሶን ውስጥ የሎቤናውያን ወገንና የሰሜአውያን ወገን ይካተቱ ነበር፤ የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሊብኒና የሺምዒ ቤተሰቦች በጌርሾን ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌድሶን የሎቤን ወገን፥ የሰሜይም ወገን ነበሩት፤ የጌድሶን ወገኖች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጌድሶን የሎቤናውያን ወገን የሰሜአውያንም ወገን ነበሩት፤ የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
እነዚህም ደግሞ የሌዊ ጐሣዎች ነበሩ፤ የሊብናውያን ጐሣ፣ የኬብሮናውያን ጐሣ፣ የሞሖላውያን ጐሣ፣ የሙሳውያን ጐሣ፣ የቆሬያውያን ጐሣ። ቀዓት የእንበረም አባት ነበረ፤
ለጌርሶን ዝርያዎች ከይሳኮር፣ ከአሴር፣ ከንፍታሌም ነገድ ጐሣዎችና ባሳን ውስጥ ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጐሣዎች ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።