ዘኍል 16:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም በእግዚአብሔር ፊት እሳትና ዕጣን ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔር የሚመርጠውም ያ ሰው ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ናችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም በጌታ ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እንዲህም ይሆናል፤ ጌታ የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ! እጅግ አብዝታችሁታል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም ላይ የከሰል ፍምና ዕጣን አድርጋችሁ ወደ መሠዊያው አቅርቡአቸው፤ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ማንኛችንን መርጦ ለራሱ እንደ ለየ እናያለን፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ሌዋውያኑ ናችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፤ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔርም የሚመርጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁንላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው፤ እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች ሆይ፥ እጅግ አብዝታችኋል ብሎ ተናገራቸው። |
እነዚህም ሙሴንና አሮንን ለመቃወም ግንባር ፈጥረው በመምጣት፣ “ምነው ከልክ አላለፋችሁም? የማኅበረ ሰቡ አባላት ሁሉ እያንዳንዳቸው የተቀደሱ ናቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ታዲያ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ የምትታበዩት ለምንድን ነው?” አሏቸው።
ቆሬንና ተከታዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ “የርሱ የሆነውና የተቀደሰው ማን መሆኑን እግዚአብሔር ጧት ያሳውቃል፤ ወደ ራሱም ያመጣዋል፤ የሚመርጠውን ሰው ወደ ራሱ እንዲቀርብ ያደርገዋል።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጧችኋል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።