እነርሱም ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንታቸው ጋራ በመሆን በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ የጌታችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዐቶች ሁሉ ለመታዘዝ በዚህ ርግማንና መሐላ ቃል ገቡ።
ነህምያ 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ወንዶች፣ ሴቶችና ማስተዋል የሚችሉ ሁሉ በተገኙበት ጉባኤ ፊት የሕጉን መጽሐፍ አመጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ሰባተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማስተዋል የሚችል ሕዝብ ሁሉ ሴት፥ ወንድ፥ ልጅ ዐዋቂው በሙሉ ወደተሰበሰቡበት ስፍራ፥ የሕጉን መጽሐፍ አመጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን በወንዶችና በሴቶች ጉባኤ፥ አስተውለውም በሚሰሙት ሁሉ ፊት አመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን በማኅበሩ በወንዶችና በሴቶች አስተውለውም በሚሰሙት ሁሉ ፊት አመጣው። |
እነርሱም ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንታቸው ጋራ በመሆን በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ የጌታችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዐቶች ሁሉ ለመታዘዝ በዚህ ርግማንና መሐላ ቃል ገቡ።
በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ አነበቡ፤ አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ፈጽሞ እንዳይገባ የሚከለክል ተጽፎ ተገኘ፤
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፣ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። እነርሱም በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛውም ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ተደረገ።
ከዚያም አገረ ገዥው ነህምያ፣ ካህኑና ጸሓፊው ዕዝራ፣ ሕዝቡንም የሚያስተምሩት ሌዋውያን፣ “ይህች ቀን ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት፤ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሏቸው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሚሰሙበት ጊዜ ያለቅሱ ነበር።
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁንላችሁ፤ በመለከት ድምፅም የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ።
“ካህኑ የሁሉ ገዥ፣ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለ ሆነ ከንፈሮቹ ዕውቀትን ሊጠብቁ፣ ሰዎችም ከአንደበቱ ትምህርትን ሊፈልጉ ይገባል፤
“ ‘በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩበት፤ ይህም የመለከት ድምፅ የምታሰሙበት ቀናችሁ ነው።
ኢያሱ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ሴቶች፣ ሕፃናትና በመካከላቸው የኖሩ መጻተኞች ባሉበት ያነበበው፣ አንድም ሳይቀር ሙሴ ያዘዘውን ቃል ሙሉ በሙሉ ነበር።