ሉቃስ 19:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ ከተማዋን አይቶ አለቀሰላት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ፥ ከተማይቱን በተመለከተ ጊዜ፥ አለቀሰላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደረሰ ጊዜም ከተማዪቱን አይቶ አለቀሰላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥ |
እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣ በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
ባትሰሙ ግን፣ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣ ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤ እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።
“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ስቦይ እፈጽምብሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።