ኢያሱ 17:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ከዚያ ፈጽመው አላባረሯቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በኀይል እየበረቱ ቢሄዱም እንኳ ከነዓናውያንን ሁሉ አላባረሩአቸውም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በረቱባቸው፤ ከነዓናውያንንም ገዙአቸው፤ ነገር ግን ፈጽመው አላጠፉአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም። |
እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።
ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።
ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከላቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።
ንፍታሌምም በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩትን አላስወጣም፤ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድሪቱ ከሚኖሩት ከነዓናውያን ጋራ ዐብረው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩት ለእነርሱ የጕልበት ሥራ ተገድደው ይሠሩ ነበር።
አሞራውያንም በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎንና በሻዓልቢም ኑሯቸውን ቀጠሉ፤ ይሁን እንጂ የዮሴፍ ወገን በበረታ ጊዜ ተገድደው የጕልበት ሥራ ከመሥራት አላመለጡም።