እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።
ኤርምያስ 48:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስራኤል ላይ ስታላግጥ አልነበረምን? ስለ እርሷ በተናገርህ ቍጥር፣ እያቃለልሃት ራስህን የምትነቀንቀውስ፣ ከሌቦች ጋራ ስትሰርቅ ተይዛለችን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንተ እስራኤል መሳቂያ አልነበረምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ቊጥር ራስህን የምትነቀንቀው በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞአብ ሆይ! እስራኤል ከሌቦች ጋር የተያዘች ባትሆንም እንኳ አንቺ እርስዋን መሳለቂያ አድርገሽ ስለ እርስዋ በተናገርሽ ቊጥር ራስሽን ትነቀንቂ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ። |
እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።
“እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?
በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ።
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነች ጊዜ ስለ ተደሰትህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፤ አንተና መላዋ ኤዶም ባድማ ትሆናላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
ስለዚህ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፤ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኰረብቶች፣ ለሸለቆዎችና ለውሃ መውረጃዎች፣ ለፈራረሱ ባድማዎችና፣ በሌሎቹ በዙሪያችሁ ባሉት ሕዝቦች ተዘርፈውና መዘባበቻ ሆነው መና ለቀሩት ከተሞች እንዲህ ይላል፤
በዚያ ጊዜ ኢየሱስ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴ እንደሚይዝ ሰው ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁ? በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ ሳስተምር አልያዛችሁኝም ነበር፤