ዳንኤል 10:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ በሐዘን ላይ ነበርኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ወራት እኔ ዳንኤል ሦስት ሳምንት ሙሉ ሳዝን ነበርሁ። |
“ወዳጆቿ የሆናችሁ ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ስለ እርሷም ሐሤት አድርጉ፤ ለርሷ ያለቀሳችሁ ሁሉ፣ ከርሷ ጋራ እጅግ ደስ ይበላችሁ።
ደግሞም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ አትፍራ፤ ማስተዋልን ለማግኘትና በአምላክህም ፊት ራስህን ለማዋረድ ከወሰንህበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የቃልህን መልስ ይዤ መጥቻለሁ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያም ጊዜ ይጾማሉ።