እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ ናታንም ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ አንዱ ሀብታም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድኻ ነበር፤
ዘካርያስ 12:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድሪቱ ላይ የእያንዳንዱ ወገን ቤተሰብ ለየራሱ ያለቅሳል፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህ ዐይነት የዳዊት ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ የናታን ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የየነገዱ ወንዶች ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህም ዐይነት የዳዊት ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱም ታለቅሳለች፥ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱም ታለቅሳለች፣ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱም ታለቅሳለች፥ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ |
እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ ናታንም ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ አንዱ ሀብታም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድኻ ነበር፤
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡና መኳንንቱ፥ መላውም የግብጽ ሕዝብ ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቁ፤ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ ስላልነበረ በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸት አስተጋባ።
ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው።
“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።
ሕዝቡን ሁሉ በአንድነት ሰብስባችሁ፥ ለተቀደሰ ጉባኤ አዘጋጁ፤ ሽማግሌዎችን ጥሩ፤ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን ጭምር ሰብስቡ፤ ሙሽራዎችም ሳይቀሩ ከጫጒላቸው ይውጡ።
የቤተ መቅደሱን ካህናትና ነቢያትን “እስከ አሁን ለብዙ ዓመቶች እንዳደረግነው በየአምስተኛው ወር በመጾም ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ማዘናችንን እንቀጥልን?” ብለው እንዲጠይቁ ነበር።
ከዚህም በኋላ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ በዚያን ጊዜ በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ያለቅሳሉ። የሰው ልጅም በኀይልና በታላቅ ክብር በደመና ላይ ሆኖ ሲመጣ ያዩታል፤
በጸሎት ለመትጋት ሁለታችሁም ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር በመለያየት አንዱ የሌላውን የጋብቻ መብት አይከልክል። በዚህም ምክንያት ራሳችሁን መቈጣጠር አቅቶአችሁ ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ እንደገና አብራችሁ ሁኑ።
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።