መዝሙር 85:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፥ እርሱን ለሚፈሩት አዳኝነቱ ቅርብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ ማዳኑ ለሚፈሩት በርግጥ ቅርብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር የሚናገረውን እሰማለሁ፥ ወደ እብደታቸው ካልተመለሱ በቀር ጌታ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ይናገራልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈጠርሃቸው አሕዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊትህም ይስገዱ፥ ስምህንም ያክብሩ፤ |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መላውን ከተማና በእዚያም በሚሰበሰቡበት ሁሉ ላይ በቀን ጥቅጥቅ ያለ ደመናን፥ በየሌሊቱም በሚንበለበለው የእሳት ብርሃን ይልካል። የእግዚአብሔርም ክብር ከተማይቱን እንደ ትልቅ ድንኳን ሸፍኖ ይጠብቃታል።
በዚህ ፈንታ እያንዳንዱ ‘እግዚአብሔር የሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር የተናገረውስ ምንድን ነው?’ በማለት ወዳጆቹንና ዘመዶቹን መጠየቅ አለበት።
ስለ እናንተ ያለኝን ዕቅድ የማውቅ እኔ ነኝ፤ ይህም ዕቅድ ክፋትን ሳይሆን ሰላምን በማስገኘት እናንተ በተስፋ የምትጠብቁት መልካም ነገር የሚፈጸምበት ነው፤
ወደ ሙታን ዓለም ወርደሽ በጥንት ዘመን ይኖሩ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር እንድትደባለቂ አደርጋለሁ፤ ከሙታን ጋር ተወዳጅተሽ እንድትኖሪ በዚያ ከምድር በታች ባለ ዓለም ውስጥ ዘለዓለም ፈራርሰው ከቀሩ ነገሮች ጋር እተውሻለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ዳግመኛ ሰው አይኖርብሽም፤ በሕያዋንም ምድር ለመኖር ቦታ የለሽም፤
እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።
ስለዚህም “ወደ መኝታህ ተመልሰህ ሂድ፤ እንደገናም የጠራህ እንደ ሆነ ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር’ በለው” ሲል ሳሙኤልን መከረው። ሳሙኤልም ተመልሶ ወደ መኝታው ሄደ።