ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።
መዝሙር 73:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥ ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት። |
ንጉሡ የሥልጣኑ ምልክት ያለበትን የማኅተም ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ ከጥሩ ሐር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አደረገለት።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ የሃመዳታ ልጅ የሆነውን አጋጋዊውን ሐማንን ከሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በላይ ክብሩን በማስበለጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው።
መራገም ልብስ የመልበስ ያኽል ይቀልለው ነበር፤ ስለዚህ የራሱ ርግማን እንደ ውሃ ወደ ሰውነቱ ገብቶ ያረስርሰው፤ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘልቆ ይግባ።
ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዕቃ ወደ ዕቃ ሳይገለባበጥ ከአተላው ጋር አብሮ የቈየ የወይን ጠጅ ጣዕሙ እንዳለ ይቈያል፤ መዓዛውም አይለወጥም፤ እንደዚሁም የሞአብ ሕዝብ አገራቸው ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሳይታወኩ ኖረዋል፤ ተማርከውም አይታወቁም።
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”
እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።
ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው።