መዝሙር 48:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤ አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤ ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤ እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ በጎች ሞት በሲኦል ይጠብቃቸዋል፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ረድኤታቸውም ከክብራቸው ተለይታ በሲኦል ትጠፋለች። |
እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።
ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ የሚናገረው የሰማውን እንጂ የራሱን ስላልሆነ እርሱ ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግራችኋል።