La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 37:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አካሄድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በእርሱ ታመን፤ እርሱም ይረዳሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከስ​ን​ፍ​ና​ዬም ፊት የተ​ነሣ አጥ​ን​ቶቼ ሸተቱ፥ በሰ​በ​ሱም፤

Ver Capítulo



መዝሙር 37:5
14 Referencias Cruzadas  

አገልጋዩም እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የእኔን ሐሳብ በመፈጸም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥ።


ዕቅድህ ሁሉ ይሳካልሃል፤ መንገድህ ሁሉ ብርሃን ይሆንልሃል።


“እግዚአብሔር ያድነው ዘንድ በእርሱ ተማምኖአልና የሚወደው ከሆነ እስቲ ያድነው” ይላሉ።


ችግርህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ከቶ ለችግር አሳልፎ አይሰጣቸውም።


የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።


ስለ ነዚህ ሁሉ ነገሮች ለረጅም ጊዜ በብርቱ ካሰብኩ በኋላ የደጋግና የጥበበኞች ሰዎችን ሥራ በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆነ ተረዳሁ፤ ስለዚህ ወደፊት የሚገጥመውን ነገር ፍቅርም ሆነ ጥላቻ አስቀድሞ የሚያውቅ ሰው የለም።


እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነው ካልሆነ በትእዛዙ አንድን ነገር ማስደረግ የሚችል ማነው?


ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ፤ ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት አይበልጥምን?


ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ።


ይልቁንስ እናንተ ማለት የሚገባችሁ “ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ነው።


እርሱ ለእናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሐሳብ ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


ሕዝቡም “ከቶ አላታለልከንም፤ አልጨቈንከንም፤ ከማንም ሰው ምንም ነገር አልወሰድክም” ሲሉ መለሱለት።