“ለእግዚአብሔር የመኖሪያ ስፍራ እስከማዘጋጅ፥ ለያዕቆብ አምላክ ቤት እስከምሠራ ድረስ፥ ወደ ቤት አልገባም፤ ወይም በአልጋ ላይ አልተኛም፤ ዕረፍት ወይም እንቅልፍ አይኖረኝም።”
“ወደ ቤቴ አልገባም፤ ዐልጋዬም ላይ አልወጣም፤
በእውነት ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥ ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም፥
በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔምም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም አዝዞአልና።
ባለህ ኀይል ሥራህን ሁሉ በትጋት ፈጽም፤ ወደ ሙታን ዓለም ከወረድህ በኋላ በዚያ ሥራና ሐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ የለም።
“ሕዝቤ ሆይ! የእኔ ቤት ፈርሶ ሳለ፥ እናንተ ተውበው በተሠሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤