መዝሙር 132:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዳዊት ዘር ንጉሥ እንዲወጣ አደርጋለሁ፤ የቀባሁትንም ኀያል አደርገዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህም ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ፤ ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ። |
ይሁን እንጂ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም በሰላም እንዲጠብቅ አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው፥
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የዳዊትን ሥርወ መንግሥት ሊያጠፋ አልፈለገም፤ ይህም የሆነው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ስለ ነበርና የዳዊት ዘሮችም ዘወትር ሳያቋርጡ የሚነግሡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተስፋ ቃል ሰጥቶት ስለ ነበር ነው።
“ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ አበረታለሁ፤ አንተም ሕዝቅኤል ሆይ! ሰዎች ሊያደምጡህ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ በዚህም ሁኔታ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”