በብርቱ ቀጥቶኛል፤ ነገር ግን እንድሞት አላደረገኝም።
መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።
መገሠጽስ ጌታ ገሠጸኝ፥ ለሞት ግን አልሰጠኝም።
ዓይኖችን ክፈት፥ ከሕግህም ድንቅ ነገርን አያለሁ።
አንተ ለእኔ ስላልታዘዝክ የኦርዮን ሚስት ስለ ወሰድክ፥ እነሆ ከቤትህ በሰይፍ የሚገደል አይጠፋም፤
በራብ ዘመን በሕይወት ያኖርሃል። በጦርነትም ጊዜ ከሞት ያድንሃል።
ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ።
ነገር ግን በኋላ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን አሁን ፈርዶ ጌታ ይገሥጸናል።
የታወቅን ስንሆን፥ እንዳልታወቅን ሆነን፥ ሞተዋል ስንባል፥ ሕያዋን ሆነን እንገኛለን፤ ብንደበደብም አልተገደልንም፤