እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና፣ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ።
ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ የእግዚአብሔርም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።
ሁሉን በሚችል አምላክ ይደሰታሉን? በየጊዜውስ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉን?
የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።
አንተ መጠጊያ ምሽጌ ነህ፤ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ የምሄድበትንም መንገድ አሳየኝ።
እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።
አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ።
ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕር መሠረት ጣልከኝ፤ በዙሪያዬም ውሃ ከበበኝ፤ ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ላይ አለፉ።
ከዚህ በኋላ፥ ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው ለማስተማር ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤
ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።
እግዚአብሔርን ተግታችሁ በማመስገን ባለማቋረጥ ጸልዩ፤