መዝሙር 105:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አገልጋዩን ሙሴንና የመረጠውን አሮንን ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሪያውን ሙሴን፣ የመረጠውንም አሮንን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጁንም አነሣባቸው። በምድረ በዳ ይጥላቸው ዘንድ፥ |
ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ሁለቱን ዕንቆች በትከሻ ላይ በሚያልፉት የኤፉድ ማንገቻዎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። በዚህ ዐይነት እኔ እግዚአብሔር ዘወትር ሕዝቤን አስታውስ ዘንድ አሮን የእነርሱን ስሞች በትከሻው ይሸከማል።
በዚያኑ ጊዜ እግዚአብሔር አሮንን “ከሙሴ ጋር ለመገናኘት ወደ በረሓው ሂድ” አለው። እርሱም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ፤ በዚያም ሙሴን አግኝቶ ሳመው።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አደርግሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን እንደ ነቢይ ሆኖ ስለ አንተ ይናገራል፤
ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።
ሳሙኤልም የሚናገረውን ቃል በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፥ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ምድር ያወጣ እግዚአብሔር ነው፤