ምሳሌ 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናገረው ቁም ነገር ስላለኝ አድምጡ፤ ከአንደበቴ ትክክለኛ ነገር ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናገረው ጠቃሚ ነገር ስላለኝ አድምጡኝ፤ ቀና ነገር ለመናገር ከንፈሮቼን እከፍታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክቡር ነገርን እናገራለሁና ስሙ፥ ከንፈሮቼም ቅን ነገርን ለመናገር ይከፈታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከከንፈሮቼም ቅን ነገርን አወጣለሁ፤ |
ይህም የሆነበት ምክንያት በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፦ “ንግግሬን በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ።”