ምሳሌ 12:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐቀኛ ምስክር በእውነት ይመሰክራል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸት ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፥ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው። |
እናንተ ልታደርጉት የሚገባ ነገር ይህ ነው፦ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በፍርድ ሸንጎዎቻችሁ ሰላም የሚገኝበትን እውነተኛ ፍርድ ስጡ።
በእርሱ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩ አንዳንድ ሰዎችንም አመጡ፤ የሐሰት ምስክሮችም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስና በሕግ ላይ የስድብ ቃል ከመናገር አይቈጠብም።
መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።