ከዚህ በኋላ ኢዮሣፍጥና ወታደሮቹ ምርኮ ለመውሰድ ወደዚያ ሄዱ፤ ብዙ የቀንድ ከብት፥ ስንቅና ትጥቅ፥ ልብስና ሌላም ውድ የሆኑ ዕቃዎች አገኙ፤ ምርኮውንም ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀባቸው፤ ነገር ግን ምርኮው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ሁሉንም መውሰድ አልቻሉም፤
ዘኍል 31:53 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር ሹማምንት ያልሆኑት ወታደሮች ግን ያመጡትን ምርኮ ለራሳቸው አስቀሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ወታደር ለራሱ የወሰደው ምርኮ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወታደሮቹም ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማረኩትን ለየራሳቸው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። |
ከዚህ በኋላ ኢዮሣፍጥና ወታደሮቹ ምርኮ ለመውሰድ ወደዚያ ሄዱ፤ ብዙ የቀንድ ከብት፥ ስንቅና ትጥቅ፥ ልብስና ሌላም ውድ የሆኑ ዕቃዎች አገኙ፤ ምርኮውንም ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀባቸው፤ ነገር ግን ምርኮው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ሁሉንም መውሰድ አልቻሉም፤
ለራሳቸው ካስቀሩት ጭምር ወታደሮቹ የማረኩት ንብረት ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፥ ሰባ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶች፥ ሥልሳ አንድ ሺህ አህዮችና፥ ሥልሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ግንኙነት ያላደረጉ ሴቶች።
ሆኖም ሴቶችንና ሕፃናት ልጆችን፥ እንስሶችንና በከተማይቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ሁሉ ለራስህ ማርከህ ትወስዳለህ፤ የጠላቶችህ ንብረት የሆነውን ሁሉ ልትጠቀምበት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ለአንተ አሳልፎ ሰጥቶሃል።