ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።
ነህምያ 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የሌላው የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ ሠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ደግሞ የሌላው የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና በርሱም ሥር የነበሩት የአገሩ ሰዎች መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ ወንድሞቻቸው፥ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዚ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ አደሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የቅዔላ ግዛት እኩሌታ ገዢ የኤንሐዳድ ልጅ ቤኒይና ወንድሞቹ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቅዒላ ግዛት እኩሌታ አለቃ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይ ወንድሞቹም አደሱ። |
ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።
በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።
የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ።