ማቴዎስ 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ቀርቦ በእጁ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩ!” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ቀርቦ ነካቸውና፣ “ተነሡ፤ አትፍሩ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም መጥቶ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፥ አትፍሩ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩም፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፦ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። |
በዚህም ጸሎት ላይ ሳለሁ በመጀመሪያው ራእይ ያየሁት ገብርኤል እኔ ወዳለሁበት ስፍራ በፍጥነት እየበረረ መጣ፤ ጊዜውም የሠርክ መሥዋዕት የሚቀርብበት ወቅት ነበር።
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤