በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
ማርቆስ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? በእግዚአብሔር ስም እለምንሃለሁ፤ እባክህ አታሠቃየኝ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቅ ድምፅ ጮኾም፣ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኔ ምን አለህ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር ይዤሃለሁ!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅ ድምፅ ጮኾም፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፤ ከእኔ ምን አለህ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር ይዤሃለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታላቅ ድምፅም እየጮኸ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅ ድምፅም እየጮኸ፦ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ፤ |
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እኔ ከጣዖቶች ጋር ምን ግንኙነት አለኝ? ለጸሎታችሁ መልስ የምሰጥና የምንንከባከባችሁ እኔ ነኝ፤ እኔ ዘወትር ለምለም ሆኖ እንደሚታይ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማ የምትሆኑትም በእኔ አማካይነት ነው።”
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ።”
ኢየሱስ ግን ዝም አለ እንጂ ምንም መልስ አልሰጠም። የካህናት አለቃውም “የቡሩክ እግዚአብሔር ልጅ መሲሕ አንተ ነህን?” ሲል እንደገና ጠየቀው።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኛ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? ልታጠፋን መጣህን? አንተ ማን እንደ ሆንክ እኔ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ።”
እናንተ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ! መልካም ነገርም አድርጉላቸው፤ ‘ብድራችን ይመለስልናል’ ብላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ይህን ብታደርጉ ዋጋችሁ ትልቅ ይሆናል፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጆችም ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለውለታ ቢሶችና ለክፉዎች እንኳ ሳይቀር ቸር ነው።
ኢየሱስን ባየ ጊዜ ጮኸ፤ በኢየሱስ ፊትም ወደቀና ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አንተ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ? እባክህ አታሠቃየኝ፤” አለው።
እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፥ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው! እነርሱ የመዳንን መንገድ ያበሥሩአችኋል!” በማለት ትጮኽ ነበር።
አጋንንትን ከሰዎች እያስወጡ በየቦታው የሚዞሩ አንዳንድ አይሁድ “ጳውሎስ በሚሰብከው በጌታ ኢየሱስ ስም እንድትወጡ እናዛችኋለን” በማለት አጋንንትን ከሰዎች ለማስወጣት ይሞክሩ ነበር።
ስለዚህ እነዚህ ልጆች ሥጋና ደም ያላቸው ሰዎች እንደ መሆናቸው ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሰው ሆነ፤ ይህን ያደረገውም በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለማጥፋት ነው፤
መልከጼዴቅ የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር፤ ይህ መልከጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን አሸንፎ ሲመለስ በመንገድ ተገናኝቶ ባረከው።
መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤
ዲያብሎስ ከመጀመሪያው አንሥቶ ኃጢአት ስለሚሠራ ኃጢአትን የሚሠራ ሁሉ የዲያብሎስ ወገን ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።
እንዲሁም ማዕርጋቸውን ባለመጠበቅ ስፍራቸውን የተዉትን መላእክት አስታውሱ፤ እነርሱን እግዚአብሔር እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በዘለዓለም እስራት፥ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጠብቆ አቆይቷቸዋል።
ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደ ቀረው ስላወቀ ዲያብሎስ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና ምድርና ባሕር ወዮላችሁ!”