ኢያሱ 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛብዲንም ቤተሰብ በየግለሰቡ ለይቶ አቀረበ፤ በመጨረሻም የዛብዲ የልጅ ልጅ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለብቻው ተለየ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ የዘንበሪን ቤተ ሰብ አባላት አንድ በአንድ ወደ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከዚያም ከይሁዳ ነገድ የሆነውም የዛራ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የከርሚ ልጅ አካን ለብቻው ተለየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱንም ሰዎች አንድ በአንድ አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የዛራ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የከርሚ ልጅ አካን ተለየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዘንበሪም ወገን ምልክት ታየ፤ የዘንበሪም ቤተ ሰብ እያንዳንዱ ተለየ፤ ከይሁዳም ወገን በሆነ በከርሚ ልጅ በዘንበሪ ልጅ በዛራ ልጅ በአካን ላይ ምልክት ታየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘንበሪም ተለየ፥ የቤቱንም ሰዎች አቀረበ፥ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሌባ በሚያዝበት ጊዜ እንደሚያፍር፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝብ ነገሥታትና መኳንንት፥ ካህናትና ነቢያት ሁሉ የምታፍሩበት ጊዜ ይመጣል።
ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።
ኢያሱም የይሁዳን ነገድ በየጐሣው አቀረበ፤ ከዚያም በኋላ የዛራሕ ጐሳ ለብቻው ተለየ፤ የዛራሕንም ጐሣ በየቤተሰቡ አቀረበው፤ የዛብዲም ቤተሰብ ለብቻው ተለየ፤