Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 14:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ሳኦልም፣ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ሳኦልም፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከልም ዕጣ ጣሉ” አላቸው። ዕጣውም በዮናታን ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሳኦ​ልም፥ “በእ​ኔና በዮ​ና​ታን መካ​ከል ዕጣ አጣ​ጥ​ሉን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕጣ ያወ​ጣ​በ​ትም ይሞ​ታል” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም” አሉት፤ ሳኦ​ልም ሕዝ​ቡን እንቢ አላ​ቸው። በእ​ር​ሱና በልጁ በዮ​ና​ታን መካ​ከ​ልም ዕጣ አጣ​ጣሉ። ዕጣ​ውም በልጁ በዮ​ና​ታን ላይ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሳኦልም፦ በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ አለ። ዮናታንም ተያዘ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 14:42
6 Referencias Cruzadas  

ሳኦልም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ ስለምን መልስ አልሰጠኸኝም? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በእነዚህ በተቀደሱ ድንጋዮች አማካይነት መልስ ስጠኝ፤ ይህን በደል የሠራነው ዮናታን ወይም እኔ ከሆንን በኡሪም አማካይነት፥ ይህን በደል የፈጸሙ ሕዝብህ እስራኤል ከሆኑ በቱሚም አማካይነት መልስ ስጠኝ።” መልሱም ዮናታንንና ሳኦልን ስላመለከተ ሕዝቡ ነጻ ሆኑ፤


ከዚህም በኋላ ሳኦል ዮናታንን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ዮናታንም “በበትሬ ጫፍ አስነክቼ ጥቂት ማር. ቀምሻለሁ እነሆ በዚህ እገኛለሁ፤ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” አለ።


በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩትም ሁሉ እርስ በርሳቸው “በዚህ አደጋ ላይ እንድንወድቅ ምክንያት የሆነው ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ።


የዛብዲንም ቤተሰብ በየግለሰቡ ለይቶ አቀረበ፤ በመጨረሻም የዛብዲ የልጅ ልጅ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለብቻው ተለየ፤


ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ይጥላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔውን የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው።


ዕጣ መጣል ጠብን ያበርዳል፤ ሁለት ጠንካራ ተከራካሪዎችንም ይገላግላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios