ኤርምያስ 7:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይልቅስ የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እርስ በርሳችሁ ቅንነት በሞላበት ፍቅር ተሳስራችሁ ኑሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታቃኑ፥ በሰውና በጓደኛው መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፥ |
የሞአብ መልእክተኞች ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምከሩን፤ በቀትር ጊዜ የእናንተ ጥላ እንደ ሌሊት ጨለማ ይከልለን።
ሌሎች ሰዎች ከሚያደርጉት ይበልጥ ምርጥ በሆነ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤትህን በመሥራትህ የተሻልክ ንጉሥ የሆንክ ይመስልሃልን? አባትህ ደስታ የሞላበት ሙሉ ዕድሜ ነበረው፤ እርሱ ዘወትር ትክክለኛና ቅን ከመሆኑ የተነሣ የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር።
“እኔ እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድና እውነት የሆነውን ነገር እንድታደርጉ አዛችኋለሁ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራ ጠብቁ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አታንገላቱ፤ በዚህም በተቀደሰ ስፍራ የንጹሕ ሰው ደም አታፍስሱበት።
አሁንም የአኗኗራችሁንና የሥራችሁን ሁኔታ ለውጣችሁ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይኖርባችኋል፤ ይህን ብታደርጉ በእናንተ ላይ ሊያመጣ ያቀደውን ጥፋት ይመልሰዋል።
በድኾች ላይ ምንም ዐይነት ግፍ ባይሠራ፥ ገንዘቡን በአራጣ አበድሮ ከፍተኛ ወለድ ባያስከፍል፥ ሕጌን ቢያከብር፥ ሥርዓቴን ቢከተል፥ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አባቱ በሠራው ኃጢአት ምክንያት አይሞትም።
ገንዘቡን በአራጣ አያበድርም፤ ወይም ከፍተኛ ወለድ አይወስድም፤ ክፉ ነገር ከመሥራት ይቈጠባል፤ ጠበኞችን ለማስታረቅ ትክክለኛ ፍርድን ይሰጣል።
ኢየሩሳሌም በልጽጋና በሕዝብ ተሞልታ በነበረችበት ጊዜ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ባሉ መንደሮች ብቻ ሳይሆን በደቡብ ክፍልና በምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ ብዙ ሕዝብ በሚኖሩበት ዘመን እግዚአብሔር በቀድሞ ነቢያቱ አማካይነት የተናገረውም ይህንኑ ቃል ነበር።
በዚህም ዐይነት በያቤሽ ገለዓድ ካሉት ኗሪዎች መካከል አራት መቶ ወንድ ያላወቁ ቆነጃጅት አገኙ፤ ስለዚህም እነርሱን በከነዓን ምድር በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ይዘው መጡ።