La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 15:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የኒምሪም ወንዞች ደርቀዋል፤ ምንም ልምላሜ ሳይቀር በአጠገቡ ያለው ሣር ደርቆአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ ሣሩ ጠውልጓል፤ ቡቃያውም ጠፍቷል፤ ለምለም ነገር አይታይም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፤ ለጋውም ጠውልጓል፤ ልምላሜውም ሁሉ የለም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኔ​ም​ሬም ውኃ ይነ​ጥ​ፋል፤ ሣሯም ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጧም ልም​ላሜ አይ​ገ​ኝም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፥ ሣሩም ደርቋል፥ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 15:6
11 Referencias Cruzadas  

ሣር ካለመገኘቱ የተነሣ፥ አጋዘን እንደ ወለደች ግልገልዋን በሜዳ ላይ ጥላ ትሄዳለች።


“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።


እነርሱ በፊታቸው የሚገኘውን ተክል ሁሉ እንደ እሳት ይበላሉ፤ እንደ ነበልባልም ያቃጥላሉ። ገና ያልደረሱበት፥ በፊታቸው ያለው ምድር፥ እንደ ዔደን የአትክልት ቦታ የለመለመ ነው፤ እነርሱ ያለፉበት ምድር ግን የወደመ በረሓ ይሆናል፤ ከእነርሱ የሚያመልጥ ምንም ነገር አይገኝም።


“ይህ እስራኤላውያን እንዲወርሱት እግዚአብሔር የረዳቸው የዐጣሮት፥ የዲቦን፥ የያዕዜር፥ የኒምራ፥ የሐሴቦን፥ የኤልዓሌ፥ የሲብማ፥ የነቦና የበዖን ከተሞች የሚገኙበት ምድር ለከብት ተስማሚ ነው፥ እኛ ደግሞ ብዙ ከብት አለን፤”


የቤትኒምራንና የቤትሃራንን ከተሞች በማደስ ለከብቶቹም በረቶችን ሠራ።


ከዮርዳኖስ ሸለቆ በተለይ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን መንግሥት ቅሬታ የሆኑትን ቤትሐራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን ተብለው የሚጠሩትን ጭምር ያጠቃልላል፤ በምዕራብ በኩል የሚዋሰናቸውም የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሆን፥ በሰሜን እስከ ገሊላ ባሕር ይደርሳል።


የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በረዶና ደም የተቀላቀለበት እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድር ሢሶ ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሢሶ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣርም ሁሉ ተቃጠለ።