La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቊጣዬን ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዤአለሁ፤ ድሌ የሚያስደስታቸውን ኀያላኔን ጠርቼአለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዝዛለሁ፤ ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ ቁጣዬንም እንዲፈጽሙ፤ ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፥ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 13:3
20 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል ሕዝቦች በፈጣሪያችሁ ደስ ይበላቸው! የጽዮን ሕዝቦችም በንጉሣችሁ ሐሤት ያድርጉ!


መንግሥታትን በማናወጥ የእግዚአብሔር ኀይል እስከ ባሕር ማዶ ደርሶአል፤ በከነዓንም ምድርም ያሉ ምሽጎች እንዲፈርሱ አዞአል።


እግዚአብሔር አሕዛብን ከሩቅ የሚጠራበት ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻ ሁሉ በመጨረሻ ይጠራቸዋል፤ እነርሱም ፈጥነው እየተጣደፉ ይመጣሉ።


‘እነሆ በስተሰሜን ወዳሉት ነገዶችና አገልጋዬ ወደ ሆነው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መልእክተኛ እልካለሁ፤ ይሁዳንና በውስጥዋ የሚኖሩትን፥ እንዲሁም በጐረቤት ያሉትን ሕዝቦች ይወጉ ዘንድ አመጣቸዋለሁ፤ ይህችን አገር ከነጐረቤቶችዋ አጠፋለሁ፤ ለማየት የሚያስፈሩና መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ ለዘለዓለም ፍርስራሽ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ከምትሰሙትም የጒምጒምታ ወሬ የተነሣ በመፍራት ወኔአችሁ አይቀዝቅዝ፤ በየዓመቱ ልዩ ልዩ የጒምጒምታ ወሬ ይነዛል፤ በምድሪቱ ላይ አንዱ ንጉሥ ሌላውን እንደሚወጋ የሚገልጥ የዐመፅ ጒምጒምታ ወሬ ይሰማል።


ባቢሎን ወደ ሰማይ ብትወጣ ከፍተኛውን ምሽግዋን ብታጠናክር እንኳ የሚደመስሳትን አጥፊ እልካለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፤ በፍጥነት ውጡ! በሸለቆውም ተሰብሰቡ።” እግዚአብሔር ሆይ፥ ተዋጊ ሠራዊትህን ላክ።


የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል።


ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!