ዘፍጥረት 48:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ወስዶ ኤፍሬምን በቀኙ ለያዕቆብ በስተግራው በኩል፥ ምናሴን በግራው ለያዕቆብ በስተቀኝ በኩል አድርጎ አቀረበለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ፣ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ፣ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፥ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አደረገው፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፤ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አቆማቸው፤ ወደ አባቱም አቀረባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ቀኝ አደረገው ወደ እርሱም አቀረባቸው። |