ዘፍጥረት 31:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “እነሆ፥ ዛሬ ይህ የድንጋይ ካብ በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ነው” አለ። ገለዓድ ተብላ የተጠራችበት ምክንያት ለዚህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም፥ “ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለ። ስለዚህም ገለዓድ ብሎ ሰየማት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “ይህች ያቆምኋት የድንጋይ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ናት” አለ። ስለዚህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ይህች ክምር በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ናት አለ። ስለዚህም ስምዋ ገለዓድ ተባለ ደግሞም ምድዻ ተባለ፦ |
በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
ለሮቤልና ለጋድ ነገዶችም ከገለዓድ እስከ አርኖን ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት ሰጠሁ፤ የደቡብ ወሰናቸውም የአርኖን ወንዝ አጋማሽ ሲሆን የሰሜን ወሰናቸው የዐሞናውያን ጠረፍ ክፍል የሆነው የያቦቅ ወንዝ ነው።
እኛ እርሱን የሠራነው በእኛና በእናንተ ሕዝብ መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር ነው፤ ይኸውም ከእኛ በኋላ ለሚነሡት ትውልዶች በተቀደሰ ድንኳኑ ፊት እግዚአብሔርን እንደምናመልክ የሚቃጠልና ሌላም መሥዋዕት፥ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት ስናቀርብ ለመኖራችን ምስክር ይሆናል፤ ይኸውም የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላችሁም’ እንዳይሉአቸው ለማድረግ ይጠቅማል፤
እንግዲህ ምናልባት ይህ ነገር ቢሆን የእኛ ዕቅድ፥ ዘሮቻችን፦ ‘ተመልከቱ! የቀድሞ አባቶቻችን የሠሩት መሠዊያ ለእግዚአብሔር ከተሠራው መሠዊያ ጋር አንድ ዐይነት ነው፤ ይኸውም በእኛና በእናንተ ሕዝቦች መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር እንጂ የሚቃጠል ወይም ሌላ መሥዋዕት እንዲቀርብበት ታስቦ አልነበረም’ ማለት እንዲችሉ ነው፤
የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት።
ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የነገረንን ቃል ሁሉ ስለ ሰማ ይህ ድንጋይ በእኛ ላይ ምስክር ነው፤ ስለዚህም አምላካችሁን ብትክዱ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችኋል።”