ዘፍጥረት 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላም ፀነሰችና ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ወንድ ልጅ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የራሔል አገልጋይ ባላም ፀነስች፤ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። |
ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
የዳን ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።