ዘፍጥረት 27:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣላት፤ እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው አድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሄዶ ጠቦቶቹን ለእናቱ አመጣላት፤ እርሷም ልክ አባቱ እንደሚወድደው ዐይነት አጣፍጣ ጥሩ ምግብ አዘጋጀችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄዶም አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም መብልን አባቱ እንደሚወድደው አደረገች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄዶም አመጣ ለእናቱም ሰጣት እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች። |
እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና “አባቴ ሆይ፥ እንድትመርቀኝ፥ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ” አለው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።