ዘፍጥረት 19:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሎጥንም ጠርተው “ከአንተ ጋር ለማደር ወደዚህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ስለምንፈልግ ወደ እኛ አውጣቸው!” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥንም ጠርተው፣ “በዚህች ምሽት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች የት አሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፥ “በሌሊት ወደ አንተ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፤ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናችው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። |
ከዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተ ጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፤ እስራኤላውያን ወደ አገሪቱ ለመግባት እየገፉ በሄዱ መጠን እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያባረራቸው አሕዛብ ይፈጽሙት የነበረውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ የይሁዳም ሕዝብ ይፈጽመው ነበር።
ከአባቱ ከአሳ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተረፉትንና በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶችና ሴቶች አመንዝራዎችን ሁሉ አስወገደ።
ለሚመለከታቸው ሰው ፊታቸው ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶም ሰዎች ሳይደብቁ ኃጢአታቸውን በግልጽ ይናገራሉ፤ በራሳቸው ላይ ጥፋትን ስላመጡ ወዮላቸው።
የበልጉም ሆነ የክረምት ዝናብ ሊቀር የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፤ አንቺ ዐይነ ዐፋርነትን አስወግደሽ እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተቢስ ሆነሻል።
ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ሠርተው ኀፍረት ተሰምቶአቸው ነበርን? እንኳንስ ሊያፍሩ ቀርቶ ዐይናቸው እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እነርሱም ይወድቃሉ፤ እኔ በምቀጣቸው ጊዜ ፍጻሜአቸው ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የእኅትሽ የሰዶም በደል ይህ ነው፤ እርስዋና መንደሮችዋ ኲራት ተሰምቶአቸው ነበር። የተትረፈረፈ ምግብና የተዝናና ኑሮ ቢኖራቸውም ችግረኞችንና ድኾችን አይረዱም ነበር።
“ሰማርያም ብትሆን የአንቺን ግማሽ ያኽል እንኳ ኃጢአት አልሠራችም፤ ከእርስዋ ይበልጥ አንቺ እጅግ አጸያፊ የሆነ ኃጢአት ሠርተሻል። የአንቺ ርኲሰት ከእኅቶችሽ ጋር ቢመዛዘን እነርሱን ከበደል ነጻ ያስመስላቸዋል።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
ለአመንዝሮችና ግብረ ሰዶምን ለሚያደርጉ፥ ሰውን አፍነው በመውሰድ ለሚሸጡ ነጋዴዎችና ለውሸታሞች፥ በሐሰት ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው፤
በዚሁ ዐይነት ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችም ሴሰኞች ሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪም ዝሙት ፈጸሙ። ስለዚህ እነርሱ በዘለዓለም እሳት ለሚቀጡት ምሳሌ ሆነዋል።
እየተደሰቱ ሳለም ከከተማይቱ የመጡ ጋጠወጦች በድንገት ቤቱን ከበው በሩን መደብደብ ጀመሩ፤ ሽማግሌውንም “ያንን ወደ ቤትህ የገባውን ሰው ግብረ ሰዶም እንድንፈጽምበት አውጣልን!” አሉት።