ዘፍጥረት 16:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም በዚያን ጊዜ 86 ዓመት ሆኖት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም፣ አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ ዕድሜው 86 ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አጋር ይስማኤልን በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ አምስት ዓመት ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ። |
ስለዚህ ሣራይ ግብጻዊት የሆነች አገልጋይዋን አጋርን ለአብራም ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው። ይህም የሆነው አብራም በከነዓን ዐሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነው።
አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤