ዘፍጥረት 13:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም ሚስቱንና ያለውን ሀብት ሁሉ ይዞ ከግብጽ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም ሚስቱንና ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከግብጽ ወደ ኔጌብ ሄደ፤ ሎጥም ዐብሮት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም ከግብጽ ወጣ፥ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም ከግብፅ ወጣ፤ እርሱና ሚስቱ፥ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ፥ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። |
ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤
በዚህ ዐይነት ኢያሱ ምድሪቱን በሙሉ፥ የተራራማውን አገር፥ ኔጌብን፥ የተራራውን ቊልቊለትና ነገሥታቱን ሁሉ ያዘ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሁሉንም ፈጀ እንጂ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት እንዲኖር አላስተረፈም።
እነርሱም የሚያጠኑት ምድር ለሰባቱ ነገድ ይከፋፈላል፤ ይሁዳ በደቡብ በኩል፥ ዮሴፍም በሰሜን በኩል የተመደበላቸውን የርስት ድርሻ ይዘው ይኖራሉ፤
አኪሽ “በዚህ ጊዜ ወረራ ያደረጋችኹት በየት በኩል ነው” ብሎ ሲጠይቀው ዳዊት “እኛ የዘመትነው ከይሁዳ በስተ ደቡብ ባለው ክፍል፥ እንደገናም በይራሕመኤል ነገድ ግዛትና ቄናውያን በሚኖሩበት ግዛት ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።