ዘፀአት 32:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ሰዎቹ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ተቀምጠው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ሕዝቡ በማለዳ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፤ የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚህም በኋላ ይበሉና ይጠጡ ዘንድ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱ ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም በነጋው ማልዶ ተነሣ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ሠዋ፤ የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረበ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ማልደው ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዉ፥ የደኅነትም መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፥ ሊዘፍኑም ተነሡ። |
ዕዳቸውን መክፈል ከማይችሉ ድኾች ላይ ልብሳቸውን መያዣ አድርገው ይወስዳሉ፤ መሥዋዕት በሚያቀርቡበትም ቦታ ሁሉ ይተኙበታል፤ ከባለ ዕዳዎች በመቀጫ ስም የወሰዱትን የወይን ጠጅ በአምላካቸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ይጠጣሉ።
የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል።
እነዚያም ሴቶች ለሞአብ ጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት እንዲመገቡ ጋበዙአቸው፤ እስራኤላውያንም የመሥዋዕቱን ምግብ በልተው ፔዖር በሚባለው ተራራ ላይ ለሚገኘው በዓል ለተባለውም ጣዖት ሰገዱ፤
“ሰዎች ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ” ተብሎ ስለ እነርሱ እንደ ተጻፈው፥ እነርሱ ጣዖትን እንዳመለኩ እናንተም እንደእነርሱ ጣዖትን አታምልኩ።
እነዚህ ሁለቱ ነቢያት የምድር ሰዎችን አስጨንቀው ስለ ነበረ በምድር የሚኖሩ ሰዎች በነቢያቱ ሞት ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።