ዘፀአት 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም የሙሴን ትእዛዝ በመፈጸም ዐማሌቃውያንን ለመውጋት ወጣ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ኢያሱ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ከአማሌቃውያን ጋራ ተዋጋ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኰረብታው ጫፍ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ሙሴ እንደ አለው አደረገ፤ ወጥቶም ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። |
ሙሴ እጆቹን ወደ ሰማይ በዘረጋ ጊዜ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጆቹን ባጠፈ ጊዜ ግን ዐማሌቃውያን እንደገና አንሰራርተው ያሸንፉ ነበር።
የሙሴ እጆች ስለ ዛሉ አሮንና ሑር ድንጋይ አምጥተው ሙሴ እንዲቀመጥበት አደረጉ፤ በግራና በቀኝ ክንዶቹን ደግፈው በመቆም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ቈዩ።
ሙሴም ለመሪዎቹ “እንደገና ወደ እናንተ ተመልሰን እስክንመጣ በዚህ ቈዩን፤ አሮንና ሑርም እነሆ፥ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ስለዚህም በመካከላችሁ ጥልና ክርክር ያለበት ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ” አላቸው።
እግዚአብሔር ትእዛዙን ለአገልጋዩ ለሙሴ ሰጠ፤ ሙሴም ለኢያሱ ሰጠ፤ ኢያሱም ትእዛዞችን ፈጸመ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ሁሉን ነገር አደረገ፤ አንዳችም አላስቀረም።