La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 10:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ግብጻውያን እርስ በርሳቸው ስለማይተያዩ ማንም ሰው እስከ ሦስት ቀን ከቤቱ መውጣት አልቻለም ነበር፤ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ አንዱ ሌላውን ማየት ወይም ከነበረበት ቦታ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር። ይሁን እንጂ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማንም ወንድሙን አላየም፥ ሦስት ቀንም ሙሉ ማንም ከስፍራው አልተነሣም፤ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማንም ወን​ድ​ሙን አላ​የም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመ​ኝ​ታው ማንም አል​ተ​ነ​ሣም፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ግን በተ​ቀ​መ​ጡ​በት ስፍራ ሁሉ ብር​ሃን ነበ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀንም ሙሉ ከስፍራው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 10:23
15 Referencias Cruzadas  

ደመናውም በግብጻውያንና በእስራኤላውያን መካከል መጥቶ ግብጻውያንን በጨለማ ሲጋርድ ለእስራኤል ሕዝብ ግን ብርሃን ይሰጥ ነበር፤ ስለዚህ የግብጽ ሠራዊት ሌሊቱን ሙሉ ወደ እስራኤላውያን መጠጋት አልቻለም።


እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን አለፈ።


አስማተኞቹ በአስማታቸው ተጠቅመው ተናካሽ ትንኝ እንዲፈላ ለማድረግ ሞከሩ፤ ነገር ግን አልተሳካላቸውም፤ ተናካሽ ትንኝም በሰዎችና በእንስሶች ላይ ተሠራጨ።


አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።


ነገር ግን በዚህ ምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር መገኘቴን ታውቅ ዘንድ በዚያን ቀን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሴምን ምድር ከዝንቦቹ መንጋ ነጻ አድርጌ እለያታለሁ።


እስራኤላውያን በሚኖሩባት በጌሴም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም።


እግዚአብሔር ግን በእስራኤላውያንና በግብጻውያን እንስሶች መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አይሞትም።


“ዕውሮችን ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ቀድሞ ባላወቁትም መንገድ እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸው የተጋረደውንም ጨለማ ወደ ብርሃንነት እለውጣለሁ፤ ወጣገባ የሆነውንም ስፍራ አስተካክላለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እኔ የምፈጽማቸው ናቸው፤ አልተዋቸውምም።


አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።


በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”


እርሱ ከጨለማ ኀይል አድኖ ወደ ተወደደው ልጁ መንግሥት እንድንገባ አድርጎናል።


እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።