ዘዳግም 1:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያች ምድር መግባት የሚችል የይፉኔ ልጅ ካሌብ ብቻ ነው፤ እርሱ በፍጹም ልቡ ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ ያቺን የጐበኛትን ምድር ለእርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይፉኔ ልጅ ከካሌብ በቀር፤ እርሱ ያያታል፥ የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ፥ ምክንያቱም ጌታን ፈጽሞ ተከትሎአል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር፥ እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ፥ ለልጆቹም እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ ብሎ ማለ። |
ካሌብ ግን በሙሴ ፊት ሕዝቡን ጸጥ በማሰኘት “እነርሱን ድል ለመንሣት የሚያስችል በቂ ኀይል ስለ አለን አገሪቱን አሁኑኑ ሄደን እንያዛት አለ።”
ነገር ግን አገልጋዬ ካሌብ ልዩ አመለካከት ስላለውና ለእኔ ያለውንም ታማኝነት ስላጸና ሄዶ የመረመራትን ምድር እሰጠዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ፤
ይህም የሆነው “ሁሉም በምድረ በዳ ይሞታሉ!” ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ ስለ ነበር ነው፤ ስለዚህም ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ሁሉም ሞተዋል።
ይህም የእግዚአብሔር ውሳኔ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸው ከታዘዙት ከቀኒዛዊው ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃልል ነው። ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው የተገኙት እነርሱ ብቻ ናቸው።