እኔም አገልጋይህ ሆንኩ ሕዝብህ እስራኤል ፊታችንን ወደዚህ ስፍራ መልሰን ስንጸልይ ጸሎታችንን ስማ፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማን፤ ይቅር በለንም።
ዳንኤል 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ስማ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ተመልከት እና ርምጃ ውሰድ! ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቷልና፣ አምላኬ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ስማ፥ አቤቱ፥ ይቅር በል፥ አቤቱ፥ አድምጥና አድርግ፥ አምላኬ ሆይ፥ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና ስለ ራስህ አትዘግይ። |
እኔም አገልጋይህ ሆንኩ ሕዝብህ እስራኤል ፊታችንን ወደዚህ ስፍራ መልሰን ስንጸልይ ጸሎታችንን ስማ፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማን፤ ይቅር በለንም።
ሕዝቤም ወደ እኔ እንዲህ በማለት ይጮኻሉ፤ ‘ምንም እንኳ የበደላችን ብዛት በእኛ ላይ ቢመሰክርም፥ እግዚአብሔር ሆይ! በተስፋ ቃልህ መሠረት እርዳን፤ ከአንተ ርቀናል፤ አንተንም አሳዝነናል።
ለምን ግራ እንደ ተጋባ ሰውና ሌላውን መርዳት እንደማይችል ኀይለኛ ወታደር ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በመካከላችን ነህ፤ በስምህም እንጠራለን፤ እባክህ አትተወን።’ ”
እነሆ፥ ጥፋትን የስሜ መጠሪያ በሆነችው ከተማ እጀምራለሁ፤ ታዲያ ከቅጣት የሚያመልጡ ይመስላቸዋልን? እኔ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ጦርነትን ስለማመጣ ከቶ ከቅጣት የሚያመልጡ የሉም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።
ነገር ግን አብረዋቸው በሚኖሩት ሕዝቦች ፊት ከግብጽ እንደማወጣቸው ለእስራኤላውያን ቃል ገብቼ ነበር፤ ስለዚህ ስሜ እንዳይነቀፍ እነርሱን ከግብጽ እንዲወጡ አድርጌአለሁ።
“እንግዲህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምልህን ሁሉ ንገራቸው፤ ከእንግዲህ ወዲህ የማደርግላችሁ ነገር በሄዳችሁበት ስፍራ ሁሉ ስላሰደባችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ እንጂ ስለ እናንተ ስለ እስራኤላውያን ብዬ አይደለም።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁን ግን የያዕቆብ ልጆች ለሆኑት ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እንደገናም አበለጽጋቸዋለሁ፤ ቅዱስ ስሜም እንዳይሰደብ እከላከላለሁ።
አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።
አንበጦቹም የምድሩን ልምላሜ ሁሉ ግጠው እንደ በሉት ባየሁ ጊዜ እኔ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ የሕዝብህን በደል ይቅር በል! ሕዝብህ እስራኤል ዐቅም ስለሌላቸው እንዴት ተቋቊመው መኖር ይችላሉ?”
አሁንም ጌታ ሆይ፤ ታላቅ በሆነውና በማይለወጠው ፍቅርህ ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ ምሕረት እንዳደረግህላቸው የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ።”
ይህም የሆነው በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በሰማይ ያሉት አለቆችና ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ጥበብ በየመልኩ እንዲያውቁ ነው።