Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 25:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነሆ፥ ጥፋትን የስሜ መጠሪያ በሆነችው ከተማ እጀምራለሁ፤ ታዲያ ከቅጣት የሚያመልጡ ይመስላቸዋልን? እኔ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ጦርነትን ስለማመጣ ከቶ ከቅጣት የሚያመልጡ የሉም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እነሆ፤ ስሜ የተጠራበትን ከተማ ማጥፋት እጀምራለሁ፤ ታዲያ ያለ ቅጣት ታመልጣላችሁን? ሳትቀጡ አትለቀቁም፤ በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ሳትቀጡ አታመልጡም፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነሆ፥ ስሜ የተጠራባት ከተማ ላይ ክፉን ነገር ማምጣት እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ ፈጽሞ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ያለ ቅጣት አትቀሩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ በላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነሆ ስሜ የተ​ጠ​ራ​ባ​ትን ከተማ አስ​ጨ​ን​ቃት ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ በውኑ እና​ንተ መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ላ​ች​ሁን? በም​ድር በሚ​ኖሩ ሁሉ ላይ ሰይ​ፍን እጠ​ራ​ለ​ሁና አት​ነ​ጹም፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነሆ፥ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፥ በውኑ እናንተ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ያለ ቅጣት አትቀሩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 25:29
19 Referencias Cruzadas  

ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?


በተራሮቼ ሁሉ በጎግ ላይ ሰይፍ እንዲመዘዝ አደርጋለሁ፤ የያንዳንዱም ሰው ሰይፍ ጓደኛውን ይበላል።


ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ሳሉ የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ክፉዎችና ኃጢአተኞች ግን እጅግ የበረታ ቅጣትን ይቀበላሉ።


አንተ ጸሎቱን ስማ፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፥ በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ የዚህን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ።


ሕዝቤ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ የመከራ ጽዋ ጠጥተዋል፤ በዙሪያው ያሉት አሕዛብ ሁሉ ከዚህ የከፋ የመከራ ጽዋ ይጠጣሉ፤ የጠጡትም ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።”


ሽማግሌ ሆነ ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥ ሕፃናትንና ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፤ ነገር ግን በግንባሩ ላይ ምልክት ያለበትን ማንንም አትንኩ፤ ግድያውንም ከዚሁ ከቤተ መቅደሴ ጀምሩ፤” ስለዚህ እዚያ በቤተ መቅደስ ከቆሙት መሪዎች አንሥተው ግድያውን ማካሄድ ጀመሩ።


“እንግዲህ መቀጣት የማይገባቸው ሰዎች እንኳ የቅጣቱን ጽዋ ገፈት የሚቀምሱ ከሆነ እናንተ ያለ ቅጣት የምታመልጡ ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እናንተም ከቅጣቱ ጽዋ መጠጣት አለባችሁ።


እንግዲህ ይህ ሁሉ ነገር በእርጥብ እንጨት ላይ የሚደረግ ከሆነ በደረቅ እንጨት ላይማ ምን ይደረግ ይሆን?”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ።


“ወይም በዚያች አገር ጦርነትን አምጥቼ ሰዎችና እንስሶች በአጥፊ መሣሪያ እንዲወድሙ ባደርግ፥


እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እኔ ራሴ ከእናንተ ጋር በመሆን አድናችኋለሁ፤ እናንተን የበተንኩባቸውን አሕዛብ ሁሉ እደመስሳለሁ፤ እናንተን ግን አላጠፋም፤ ሆኖም ያለ ቅጣት አልተዋችሁም፤ የምቀጣችሁ ግን እንደ ጥፋታችሁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ከዚህ በኋላ እኔ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ እስከሚሰክሩ ድረስ በወይን ጠጅ ልሞላቸው እንዳቀድኩ ንገራቸው፤ በዚያን ጊዜ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታትን፥ ካህናትን፥ ነቢያትንና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን ሁሉ በወይን ጠጅ አሰክራቸዋለሁ።


ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “በኢየሩሳሌምና በጽዮን ተራራ የማደርገውን ሁሉ ከፈጸምኩ በኋላ ስለ ትምክሕቱና ስለ ትዕቢቱ ሁሉ ብዛት የአሦርንም ንጉሠ ነገሥት ደግሞ እቀጣለሁ።”


በድኾች ብታፌዝ የፈጠራቸውን እግዚአብሔርን እንደ ሰደብክ ይቈጠራል፤ በሌላው ሰው ላይ በሚደርሰው መከራ ብትደሰት አንተም ትቀጣለህ።


በእርግጥ ክፉ ሰዎች መቀጣታቸው የማይቀር ነው፤ ደጎች ግን ይድናሉ።


‘የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ እነሆ በጆሮው ለሚሰማው ሰው ሁሉ የሚዘገንን መቅሠፍት አመጣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios