Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይህንንም የማደርገው የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ እኔን እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣ ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም ሁሉ እንዲሹኝ ነው፤ እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን እንዲፈልጉ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የቀ​ሩት ሰዎ​ችና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:17
32 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ብዙ የአሕዛብ ነገዶች ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው ወገኖቹ ይሆናሉ። እርሱም በመካከላችሁ ይኖራል፤ እኔንም ወደ እናንተ የላከኝ እርሱ መሆኑን ትገነዘባላችሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።


ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።”


እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።


እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤


እነርሱ በስሜ የተጠሩና ለክብሬ የፈጠርኳቸው በእጄም የአበጀኋቸውና የሠራኋቸው ሕዝቤ ናቸው።”


ለምን ግራ እንደ ተጋባ ሰውና ሌላውን መርዳት እንደማይችል ኀይለኛ ወታደር ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በመካከላችን ነህ፤ በስምህም እንጠራለን፤ እባክህ አትተወን።’ ”


በዚያን ጊዜ የእሴይ (የዳዊት) ዘር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ ሕዝቦች እርሱን ይፈልጉታል፤ መኖሪያውም የተከበረ ይሆናል።


‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።


ትእዛዜን ስለ ፈጸምክ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።”


ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።


በዚህም ዐይነት ከኤዶም ምድር የተረፉትንና ሌሎችንም በስሜ የተጠሩትን ሕዝብ ሁሉ ይወርሳሉ፤” ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።


የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።”


እግዚአብሔር ሆይ! ስማን! እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን! እባክህ አድምጠን! ሥራህንም ግለጥ! አምላክ ሆይ! አትዘግይ፤ ይህች ከተማና ይህ ሕዝብ በስምህ የተጠሩ ናቸው።”


በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ዘንድ ኢምንት ናቸው፤ በሰማይ መላእክትም ሆነ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ የፈቀደውን ያደርጋል፤ ፈቃዱን እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ወይም ‘ምን እያደረግህ ነው’ የሚለው ማንም የለም።


በመጨረሻም በለዓም የሚከተለውን የትንቢት ቃል ተናገረ፤ “በሰሜን በኩል የተሰበሰበ ይህ ሕዝብ ማን ነው?


ደግሞም እግዚአብሔር “በዚህ ሁኔታ ስሜን ጠርተው የእስራኤልን ሕዝብ ቢባርኩ፥ እኔም እነርሱን እባርካቸዋለሁ” አለው።


እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”


ከዚያን በኋላ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የእግዚአብሔር ወገን መሆንክን አይተው ይፈሩሃል።


እኛ በአንተ እንዳልተገዙና በስምህ እንዳልተጠሩ ወገኖች ከሆንን ብዙ ጊዜአችን ነው።


እናንተ የምትጠሩበትን ያን ክቡር ስም የሚሰድቡስ እነርሱ አይደሉምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios