ዳንኤል 4:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕዝብ መካከል ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ኑሮህም ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠል ትረሰርሳለህ፤ ይህም ሁሉ የሚደርስብህ ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስከምትረዳ ድረስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝብ ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ዱር አራዊትም ጋራ ትኖራለህ። እንደ ከብት ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠልም ትረሰርሳለህ፤ ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልዑሉም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለሚወድደውም እንዲሰጠው እስክታውቅ ድረስ ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ፥ መኖሪያህም ከምድር አራዊት ጋር ይሆናል፥ እንደ በሬም ሣር ትበላ ዘንድ ትገደዳለህ፥ በሰማይም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ሰባት ዘመናትም ያልፉብሃል። |
‘በታላቁ ኀይሌና ብርታቴ ዓለምንና የሰውን ዘር እንዲሁም በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሶችን ሁሉ ፈጠርኩ፤ ምድርንም የሚገዛ ማን እንደሚሆን እወስናለሁ።
እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው።
ንጉሡም ዳንኤልን “የአንተ አምላክ ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ አምላክ ነው፤ የነገሥታት ሁሉ ጌታ ነው፥ ምሥጢርንም ሁሉ መግለጥ የሚችል ነው፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ታላቅ ምሥጢር ለመግለጥ ችለሃል” አለው።
ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’