ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ሐዋርያት ሥራ 8:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም ሄደ፤ እነሆም፥ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ከሹሞችዋ የበለጠ፥ በሀብቷም ሁሉ ላይ በጅሮንድ የነበረ፥ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ነበር፤ እርሱም ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ |
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ለእኔ በመታዘዝ የሚያገለግሉኝን ሕዝቦች በምመዘግብበት ጊዜ ግብጽንና ባቢሎንን እጨምራለሁ፤ ከኢየሩሳሌም ተወላጆች ጋር የፍልስጥኤምን፥ የጢሮስንና የኢትዮጵያን ሕዝቦች እጨምራለሁ።
የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፥ ቆዳቸው ለስላሳ፥ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፥ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ።
“ወንዶች ልጆቼ ከሩቅ አገር እንዲመጡ በሰሜን በኩል ያሉትን አገሮች ተዉአቸው፥ በደቡብ በኩል ያሉትን አገሮች ‘አትያዙአቸውም’ ብዬ አዛለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።
ኢትዮጵያዊ መልኩን፥ ነብርም ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ አይችልም፤ እንዲሁም እናንተ ክፉ ነገር ማድረግን ስለ ለመዳችሁ ደግ ሥራ መሥራት አይሆንላችሁም።
የሆነ ሆኖ አቤሜሌክ ተብሎ የሚጠራ በቤተ መንግሥቱ ያገለግል የነበረ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ እኔን ወደ ጒድጓድ ውስጥ እንደ ከተቱኝ ሰማ፤ በዚያን ጊዜ ንጉሡ በብንያም ቅጽር በር ሸንጎ ተቀምጦ ነበር፤
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “ልክ ከዚህ በፊት እንደ ተናገርኩት በዚህች ከተማ ላይ ብልጽግናን ሳይሆን ጥፋትን አመጣለሁ፤ በዚህችም ከተማ ሆነህ ይህ ሁሉ ሲፈጸም በዐይንህ ታያለህ፤
የደቡብ ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለ መጣች በፍርድ ቀን ከዚህ ዘመን ትውልድ ጋር ተነሥታ በእርሱ ላይ ትፈርድበታለች፤ አሁን ግን ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።”
‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።