እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
2 ጢሞቴዎስ 2:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነትን ወደ ማወቅ ይደርሱ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ንስሓን እንደሚሰጣቸው ተስፋ በማድረግ የሚቃወሙትን በየዋህነት የሚያቃና መሆን ይኖርበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትዕግሥተኛና የሚቃወሙትን በየዋህነት የሚገሥጽ ሊሆን ይገባዋል። ከዚህም የተነሣ ምናልባት እግዚአብሔር ንስሓ ገብተው እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲመጡ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም “ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ፤” ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም፦ ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሐን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው፥ ወደ አእምሮ ይመለሳሉ ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ። |
እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤
አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ አዲስ መንፈስንም በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ከሰውነታቸው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣቸዋለሁ።
“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ! የስደት ዕቃህን ጠቅልለህ አዘጋጅ፤ እነርሱ እያዩም የስደት ጒዞህን በቀን ጀምር፤ እንደ ስደተኛ ከቦታህ ተነሥተህ ወደ ሌላ ቦታ ሂድ፤ ዐመፀኞች ቢሆኑም እንኳ ያስተውሉ ይሆናል።
አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ።
መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
መጥምቁ ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ ቢመጣ አላመናችሁትም፤ ኃጢአተኞችና ዘማውያን ግን አመኑት፤ ይህንንም አይታችሁ እንኳ ንስሓ ገብታችሁ አላመናችሁትም።”
እነርሱም ይህንን በሰሙ ጊዜ የሚመልሱትን አጥተው ዝም አሉ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔር ለአሕዛብም ለአዲስ ሕይወት የሚያበቃቸውን ንስሓ ሰጥቶአቸዋል፤” በማለትም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤
ሐዋርያቱም ትእዛዙን ተቀብለው በማለዳ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና ማስተማር ጀመሩ። በዚያን ጊዜ የካህናት አለቃውና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው የሸንጎውን አባሎችና የአይሁድ ሽማግሌዎችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡአቸው ሰዎችን ወደ ወህኒ ቤት ላኩ።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ተሳስቶ አንዳች ጥፋት አድርጎ ቢገኝ መንፈሳውያን የሆናችሁት እናንተ እንዲህ ዐይነቱን ሰው በገርነት አቅኑት፤ ነገር ግን አንተም በዚህ ዐይነት ፈተና እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፥ መንፈሳዊነትን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ በትዕግሥት መጽናትን፥ ገርነትን ተከታተል።
የእግዚአብሔር አገልጋይና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው፥ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች ለማጠንከርና የሃይማኖትንም እምነት ሙሉ በሙሉ እንዲያውቁ ለማድረግ ከተሾመ ከጳውሎስ የተላከ፦
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።
ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየው ይጸልይለት፤ የሰውዬው ኃጢአት ለሞት የማያደርስ ከሆነ እግዚአብሔር ሕይወትን ይሰጠዋል። ነገር ግን ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ። ለእንዲህ ዐይነቱ ኃጢአት ይጸልይ አልልም።