ነገር ግን ለእነርሱ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ያዝ፤ አፉንም ስትከፍት በውስጡ ገንዘብ ታገኛለህ፤ ያንንም ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል።”
2 ቆሮንቶስ 6:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ በምንም ነገር ለማንም መሰናከያ አንሆንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ ለማንም ዕንቅፋት መሆን አንፈልግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በማናቸውም መንገድ አንዳች ዕንቅፋት አናኖርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ፥ በአንዳች ነገር ማሰናከያ እንዳንሰጥ እንጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። |
ነገር ግን ለእነርሱ እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ያዝ፤ አፉንም ስትከፍት በውስጡ ገንዘብ ታገኛለህ፤ ያንንም ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል።”
“ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢጣልና ቢሰጥም ይሻለዋል።”
በዚህ ዐይነት ይህ የእኛ ሥራ መናቁ ነው፤ ይህም ብቻ ሳይሆን በእስያና በመላው ዓለም ሰው ሁሉ የሚያመልካት የታላቂቱ አምላክ የአርጤሚስ ቤተ መቅደስ ከንቱ ሆኖ መቅረቱ ነው፤ የእርስዋም ታላቅነት መሻሩ ነው።”
ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።
የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።