1 ሳሙኤል 8:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ዐይነት ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት እኛን የሚያስተዳድርና ከጠላቶቻችንም ጋር በምንዋጋበት ጊዜ ወደ ጦር ሜዳ የሚመራን ንጉሥ ይኖረናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፣ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፥ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፤ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፤ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላታችንን ይዋጋል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም ደግሞ እንደ አሕዛብ ሁሉ እንሆናለን፥ ንጉሣችንም ይፈርድልናል፥ በፊታችንም ወጥቶ ስለ እኛ ይዋጋል አሉት። |
ከእኛ ጋር የማትወጣ ከሆነ በሕዝብህም ሆነ በእኔና በሕዝብህ ደስ መሰኘትህን ሰዎች ሁሉ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ? እኛን በምድር ላይ ካሉት ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተለየ የሚያደርገን የአንተ ከእኔና ከሕዝብህ ጋር መሆን አይደለምን?”
እኔ እነርሱን ከነዚህ ከፍተኛ አለቶች ላይ ሆኜ አያቸዋለሁ፤ ከኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከታቸዋለሁ፤ እነርሱ ለብቻቸው የሚኖሩ ሕዝብ ናቸው። እነርሱ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የተለዩ መሆናቸውን ያውቃሉ።
የዓለም ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን በወደደ ነበር፤ ነገር ግን የዓለም ስላልሆናችሁና እኔ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኳችሁ፥ ዓለም ይጠላችኋል።
አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ንጉሣችሁ ሆኖ ሳለ የአሞን ንጉሥ ናዖስ በእናንተ ላይ መነሣቱን ባያችሁ ጊዜ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ የሚመራችሁ ንጉሥ አግኝቼአለሁ፤ እኔ ግን ዕድሜዬ ስለ ገፋ ሸምግዬአለሁ፤ ልጆቼም ከእናንተው ጋር አሉ፤ ከወጣትነት ጊዜዬ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የእናንተ መሪ ሆኜ ቈይቼአለሁ።
“እነሆ! አንተ በእርጅና ላይ ነህ፤ ልጆችህም የአንተን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ስለዚህ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው እኛን የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን።”