1 ሳሙኤል 28:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ብዛት ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም ተሸበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተሸበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተሸበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ባየ ጊዜ ፈራ፥ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ። |
ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ።
ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም።